Search

ከኋላ ቀር የአገልግሎት አሰጣጥ ለመውጣት የሚያስችሉ ሥራዎች እየተሠሩ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

እሑድ መስከረም 18, 2018 92

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ የግልፀኝነት እና ተጠያቂነት ችግሮች ያሉበት በመሆኑ በርካታ ቅሬታዎችን ሲያስነሳ መቆየቱን ተናግረዋል።
መንግሥት የሕዝብ አንገብጋቢ ችግሮች ብሎ ከለያቸው መካከል የአገልግሎት አሰጣጥ አንዱ ነው ብለዋል።
ችግሩን ለመፍታት የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልገሎት ተግባራዊ መደረጉንም አስታውቀዋል።
ከኋላ ቀር የአገልግሎት አሰጣጥ በመውጣት ዓለም የደረሰበትን ስልጡን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ሥራዎች በክልሉ እየተከናወኑ እንደሆነም ገልጸዋል።
በአማራ ክልል በሚገኙ ከተሞች የመሰቦ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ለማስፋፋት እየተሠራ መሆኑንም አስታውቀዋል።
በቀጣይም በደሴ እና ጎንደር ከተሞች መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ወደ ሥራ ለማስገባት ዝግጅቶች እየተደረጉ ስለመሆኑም አመላክተዋል።
የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት በቅንጅት የሚሳለጥ በመሆኑ የተልዕኮ መደራረብ እና አሰራር ግድየለሽነትን በማስወገድ የተገልጋዮችን ጊዜ፣ ገንዘብ እና ጉልበትን የሚቆጥብ ስለመሆኑ ተናግረዋል።
በሳሙኤል ወርቃየሁ