Search

ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሳለች - የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር

ሰኞ መስከረም 19, 2018 57

በስዊዘርላንድ፣ ጄኔቫ በተካሄደው የዓለም የንግድ ድርጅት 6ኛ የሥራ ቡድን ስብሰባ ኢትዮጵያ ፍሬያማ ቆይታ ማድረጓን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ተናገሩ።

ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ኢትዮጵያ በስብሰባው ያደረገችውን ተሳትፎ በተመለከተ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ ነው።

እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ፥ ኢትዮጵያ የድርጅቱ አባል እንድትሆን 30 ሀገራት ድጋፍ የሰጡ ሲሆን፤ የዓለም ባንክም በ31ኛነት ለኢትዮጵያ አባልነት ድጋፉን ሰጥቷል።

በስብሰው፥ ከሥራ ቡድኑ አባላት ለተነሱ ከ200 በላይ ጥያቄዎች ምላሽ የተሰጠ ሲሆን፤ ይህን ተከትሎም የሥራ ቡድኑ የኢትዮጵያን የፍሬ ነገር ሪፖርት ወደ ሥራ ቡድን ረቂቅ ሪፖርት ከፍ አድርጓል።

በዚህም ኢትዮጵያ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሳለች ያሉት ሚኒስትሩ፤ የዓለም ንግድ ድርጅት 6ኛ የሥራ ቡድን ስብሰባ ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ ለድርጅቱ አባልነት መቃረቧ የታየበት መሆኑን አክለዋል።

ከዚህም ባሻገር ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ድርድር ከ14 ሀገራት ጋር ያደረገች ሲሆን፤ ከእነዚህ ውስጥ ከ6 ሀገራት ጋር ስምምነት ላይ ተደርሷል ነው ያሉት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)።

በብሩክታዊት አስራት

#EBCdotstream #Ethiopia #WTO