ቻይና ባህር ውስጥ ነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝን በማውጣት ጥቅም ላይ እያዋለች ይገኛል።
ሀገሪቷ ባህር ውስጥ የዘረጋችው የነዳጅ እና የጋዝ ማስተላለፊያ የቧንቧ መስመር አጠቃላይ ርዝመቱ 10 ሺ ኪሎ ሜትር ማለፉን አስታውቃለች።
የባህር ጨው እና የተለያዩ ኬሚካሎችን ተቋቁሞ ለዓመታት የሚቆየውን ይህ ግዙፍ የባንቧ መስመር ለማምረት እና ለመዘርጋት ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ወሳኝ ድርሻ እንዳላቸው ተጠቁሟል።
ቻይና ባለፉት 5 ዓመታት ባህር ውስጥ የዘረጋቻቸው የነዳጅ እና የጋዝ ማስተላለፊያ ቧንቧዎች ከ2 ኢንች እስከ 48 ኢንች የሚደርስ ስፋት እንደአላቸው ሲጂቲኤን ዘግቧል።
በጌትነት ተስፋማርያም