Search

ኢትዮጵያ በመድኃኒት ቁጥጥር ከዓለም ጤና ድርጅት 3ኛ ደረጃ የብቃት ማረጋገጫን አገኘች

ረቡዕ መስከረም 21, 2018 41

ኢትዮጵያ በመድኃኒት ቁጥጥር ከዓለም ጤና ድርጅት 3 ደረጃ (ማቹሪቲ ሌቭል-3) የብቃት ማረጋገጫን አግኝታለች፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት የሀገራት የህክምና ምርቶች ተቆጣጣሪ አካላት የቁጥጥር ስርዓት የደረሰበትን ደረጃ በመገምገም ደረጃ ይሰጣል፡፡

በዚህምኢትዮጵያ በመድኃኒት ቁጥጥር ከዓለም ጤና ድርጅት 3 ደረጃ የብቃት ማረጋገጫን ማግኘት ችላለች፡፡

ኢትዮጵያ ያገኘችው ደረጃ፤ በመድኃኒት ቁጥጥር የተረጋጋና የተቀናጀ ሥርዓት ላይ መድረሷን የሚያመላክት ሲሆን፤ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ መድኃኒቶች ጥራት፣ ደህንነትና ውጤታማነት በዓለም አቀፍ ደረጃ መረጋገጡን የሚያሳይ ነውም ተብሏል፡፡

የጤና ሚኒስቴር፤ ይህንን ደረጃ ለማሳካት ከፍተኛ ጥረት ላደረጉ የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን እንዲሁም ሌሎች አጋር አካላት ምስጋና አቅርቧል።

የህብረተሰባችንን ጤና ለመጠበቅ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው ጠንካራ የጤና ቁጥጥር ስርዓት ለመፍጠር እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ሲልም መልእክቱን አስተላልፏል፡፡

#ebc #ebcdotstream #Ethiopia #WHO #ML3