ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ትናንሽ ችግሮችን በትናንሽ መፍትሄዎች መፍታት ችግሩን መከተል ነው ሲሉ ተናግረዋል።
በመደመር መንግሥት እንዳስቀመጥነው ትናንሹን ችግር በትላልቅ ጉዳይ መፍታት መዝለል ነው፤ ችግር እንዳይከተለን ማድረግ ነው ሲሉ ነው የተናገሩት።
የሩሲያ እና የቻይና ዕድገት የሚያሳየውም ይህንኑ መሆኑን አስረድተው፤ ኢትዮጵያ የጀመረቻቸው ሜጋ ፕሮጀክቶች ችግሮች እንዳይከተሉን እና ችግሮቹን እንድንዘል የሚያደርጉ ናቸው ሲሉ ገልፀዋል።
130 ሚሊዮን ሕዝብ ያላት ኢትዮጵያ በትናንትናው መንገድ ተንፏቃ ችግሯን መቅረፍ እና የበለፀገች ሀገር መሆን አትችልም ነው ያሉት ተቅላይ ሚኒስትሩ።
ከገባንበት ጥልቅ እንቅልፍ ሕዳሴ በንጋት አንቅቶናል፤ ሀገር ወዳድ ከሆኑት ጋርም ተሰናስለን ግዙፍ ፕሮጀክቶችን እናስቀጥላለን ብለዋል።
በጋራ የምንበለፅግ ስለሚያደርገን በጀመርነው ትላልቅ ነገር የማሳብ፣ የመጀመር፣ በፍጥነት የመጨረስ እንዲሁም ውጤት የማስገኘት ልምዳችን ብልፅግናን እንድናሳካ ለመላው የምስራቅ አፍሪካ ዜጎች ጥሪዬን ማስተላለፍ እወዳለሁ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።
በጌትነት ተስፋማርያም