Search

እነሱ ይዋሻሉ እኛ እንሠራለን፤ እነሱ ያወራሉ እኛ እንከናወናለን፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ዓርብ መስከረም 23, 2018 151

ተግተን ጀምረን እንድንጨርስ ተግተው የሚዋሹ ያስፈልጋሉ፤ እነሱ ይዋሻሉ እኛ እንሠራለን፤ እነሱ ያወራሉ እኛ እንከናወናለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
በሥራዎቻችን ሁሉ ኢትዮጵያን ከፍ እናደርጋለን፤ ብልፅግናን እናረጋግጣለን፤ ይህ እስኪሆን ድረስ አንተኛም ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለዋል።
አፍሪካን የሚያነቃቃው እና የሚያበረታታው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ከተመረቀ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ፣ ትናንት የተመረቀውን የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝን ጨምሮ 10 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ኢንቨስትመንት በሶማሊ ክልል ለማስጀመር እና ለማስመረቅ ተችሏል ብለዋል።
ይህ ለሶማሊ የወጣው የብልጽግና ፀሐይ፣ ብርሃኑ በመላ ኢትዮጵያ እስኪረጋገጥ እንዲሁም እያንዳንዱን ዜጋ ካለበት ድህነት አውጥቶ ወደሚገባው የብልጽግና ደረጃ እስኪደርስ በትጋት መስራት ይገባናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
ለዚህም ህዝብ እና መንግሥት አንድ ላይ በመሆን በትጋት መስራት እና መጨረስ እንደሚኖርባቸው ነው የገለጹት።
በቢታንያ ሲሳይ