Search

ሕልማችን ሩቅ ነው፤ ተስፋችን የሚጨበጥ ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ዓርብ መስከረም 23, 2018 72

ሕልማችን ሩቅ ነው፤ ተስፋችን የሚጨበጥ ነው፤ የምግብ ሉዓላዊነትን በኢትዮጵያ ውስጥ እናረጋግጣለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሶማሊ ክልል የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ሲያስመርቁና ግንባታ ሲያስጀምሩ ባደረጉት ንግግር፤ የሶማሊ ክልል ከራሱ አልፎ ቀጠናውን መመገብ የሚችል አቅም እንዳለው ጠቅሰዋል፡፡
ክረምት ከበጋ ወንዝ የሚፈስበት አስደማሚው የጎዴ አካባቢ መሬት፣ ትንሽ ማሽንና ማዳበሪያ ቢያገኝ እንኳን ኢትዮጵያን ቀጣናውን ሊመግብ ይችላል ብለዋል፡፡
በመሆኑም የሶማሊ ክልል አመራሮች ቀን መጥቶላችኋል፤ ዕድል አግኝታችኋል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
ይህ ዕድል ሳይባክን በአንድ ልብ በአንድ መንፈስ ተባብረን የሶማሊን ክልል ለሶማሌ ብቻ ሳይሆን ለምሥራቅ አፍሪካ የሚተርፍ ልማት ያለበት ክልል እንድናደርግ አደራ ልላችሁ እፈልጋለሁ ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በቢታነተያ ሲሳይ