Search

የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

ዓርብ መስከረም 23, 2018 43

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው፤ ኢሬቻ የምስጋና በዓል ነው ብለዋል፡፡

ኢሬቻ ይበልጡንም ምድርን በዝናብ ያጠገበው ፈጣሪ በምስጋና የሚዘከርበት በዓል እንደሆነም ገልፀዋል።

የኦሮሞ ሕዝብ በዚህ ውብና በተስፋ በተሞላ ወቅት የክረምቱን አስቸጋሪ ጊዜ አሳልፎ በሁሉም ነገር ወደተትረፈረፈ ብራ ላሻገረው ፈጣሪ ዐደባባይ ወጥቶ ምስጋና ያቀርባል፤ ያለፈውን ዘመን ዘግቶ አዲስ ዘመን ይጀምርበታል ሲሉም ጠቅሰዋል።

የምስጋና ባህል እንዲገነባ፣ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት እንዲጸና፣ ኢትዮጵያ ከሁሉም- በሁሉም- ለሁሉም እንድትሆን እሬቻ አንዱ ዕሴት መሆኑንም ጠቁመዋል።

#ebc #ebcdotstream #Ethiopia #Irreecha