መንግስት የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ከፌደራል እስከ ታችኛው የመንግስት ማዋቅር በኃላፊነት እንዲሰሩ እና በሀገር ግንባታ አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ እያደረገ ይገኛል፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በፌደራል ደረጃ የካቢኔ አባል በመሆን በሚኒስትሮች ምክር ቤት ከፍተኛ አመራር በመስጠት እየተሳተፉ ናቸው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት ምረቃ ስነ ስርዓት ላይ፤ "ተደምረን ኢትዮጵያን ማበልፀግ በመቻላችን ለፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ለዶ/ር በለጠ ሞላ እንኳን ደስ አላችሁ" ብለዋል፡፡
ሁለቱ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ሚኒስትሮች ከመሆናቸውም በላይ ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ለውጥ ምሶሶ ጣዮች ናቸው ሲሉም ጠቁመዋል፡፡
በጋራ በሰጠነው አመራር ለተገኘው ሀገራዊ ስኬት እንኳን ደስ አላችሁ በማለትም አድናቆታቸውን ገልፀዋል፡፡
የሁለቱ ሚኒስተሮች ቁርጠኝነት፣ ትጋትና፣ የአመራር ተሳትፎ፤ ለኢትዮጵያ ፖለቲካ መታደስ፤ መቀየር መሰረት የሚጥል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ተደምረን ኢትዮጵያን ማበለፀግ ችለናል ብለዋል፡፡
ሁሉም ሀገራዊ ፍላጎቶቻችን የሚሳኩት በኢትዮጵያውያን የተደመረ ጥረትና ትጋት እንጂ በልመና አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለሀገራችን ሁለንተናዊ ብልፅግና ልንተባበር፣ በጋራ ልንቆም ይገባል ሲሉም ተናግረዋል፡
በላሉ ኢታላ
#EBC #ebcdotstream #Ethiopia #PMAbiyAhmed