ኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ እሴቱን ጠብቆ በአባገዳዎች መሪነት ንጋት ላይ በአዲስ አበባ በድምቀት ይከበራል።
የበዓሉ ታዳሚዎችም እየጨፈሩ እና ምስጋና እያቀረቡ በዓሉ ወደሚከበርበት ኢሬቻ ፓርክ እየገቡ ይገኛሉ።

ኢሬቻ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ከጥንት ቅድመ አያቶቹ ጀምሮ ሕዝቡ ለፈጣሪ ምስጋና የሚያቀርብበት እና ሰላም የሚያጠናክርበት፣ ይቅርታ እና እርቅ የሚፈፀምበት በዓል ነው።

ኢሬቻ የኅብረብሔራዊነት ማጠናከሪያ እንዲሁም የመቻቻል እና የአብሮነት ምልክት ነው።
በዓሉ ኢትዮጵያውያን በመካከላቸው እህትማማችነት እና ወንድማማችነትን የመያጠናክሩበትም ጭምር ነው።
ሆረ ፊንፊኔ እሴቱን ጠብቆ በነገው እለት በአባገዳዎች መሪነት የሚፈፀም ይሆናል።
በላሉ ኢታላ
#EBC #Irreecha #Ethiopia #HoraFinfinnee