የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ ‘የኢሬፈና’ /ምስጋና የማቅረብ/ ሥነ-ሥርዓት በአባገዳዎች ምርቃት በአዲስ አበባ ኢሬቻ ፓርክ መከናወን ጀምሯል።
አባገዳዎቹ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በቅደም ተከተል የምርቃት ሥነሥርዓቱን አከናውነዋል።
እናቶች እና አባቶች፣ ቄሮ እና ቀሬዎች ለምለም ሳር እና አደይ አበባ ይዘው “መሬ ሆ…!” እያሉ ታላቅ እልልታ እና ምስጋና አቅርበዋል።
ሁሉም የበዓሉ ተሳታፊዎች “ሆ ያ መሬ ሆ …” እያሉ ጭጋጉ መገፈፉን፣ ፈጣሪያቸው ምሕረት ማድረጉን ከዘመን ዘመን ማሸጋገሩን አብስረዋል።
ኢሬቻ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ከጥንት ቅድመ አያቶቹ ጀምሮ ሕዝቡ ለፈጣሪ ምስጋና የሚያቀርብበት እና ሰላም የሚያጠናክርበት፣ ይቅርታ እና እርቅ የሚፈፀምበት በዓል ነው።
በላሉ ኢታላ