Search

ለሀገር ውስጥም ለዓለም አቀፍ ኩነቶች ተመራጭ የሆነችው አዲስ አበባ

ቅዳሜ መስከረም 24, 2018 301

በአዲስ አበባ ከተማ አለም አቀፍ እና አህጉራዊ ኩነቶች፣ የአደባባይ ክብረ በአሎች በብቃት የማስተናገድ አቅም እያደገ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገለፀ። 

አዲስ አበባ የአደባባይ በዓሎችንና ትላልቅ ኩነቶችን የማስተናገድ አቅሟ እያደገ የመጣ እና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚቀመጥ መሆኑን የከተማዉ አስተዳደር ከፍተኛ አመራር ገምግሟል፡፡

በከተማዋ የተካሄዱት የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ፣ የአፍሪካ ካረቢያን መሪዎች ጉባኤ፣ የህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ ህዝባዊ ሰልፍ፣ የመስቀል ደመራ፣ ኢሬቻን በተሳካ ሁኔታ መስተናገዳቸው ትልቅ ትርጉም የሚሰጠዉ መሆኑን በግምገማው ተጠቁሟል።

የልማት ስራዎችና መሰረተ ልማቶች ወደ አደባባይ ለሚተመዉ ነዋሪና ጎብኚ የሚፈጥሩት ተጨማሪ ዉበት እና ምቾት አዲስ አበባን የስህበት ማዕከል ማድረጉንም በግምገማው ተገልጿል።

የአለም አቀፍና የአገር ዉስጥ ጎብኚዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩንም ተመላክቷል። 

በዋናነት የከተማው ህዝብ በኃላፊነት ስሜት፣ በሃይማኖት፣ በብሄር፣ በፓለቲካ አቋም ሳይለያይ በወንድማማችነትና እህትማማችነት መንፈስ ከመንግስት ጋር በሁሉም መስክ መስራቱ ከፍተኛ ሚና መጫወቱም ነው የተገለፀው። 

በመተባበርና በመደጋገፍ የተመዘገበው ስኬት ለኢትዮዽያ ትልቅ የአብሮነትና የማንሰራራት መሰረት ስለሆነ ይበልጡን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ተጠቅሷል።