Search

የኢሬቻ ሆረ ሀርሰዴ ‘ኢሬፈና’ /ምስጋና የማቅረብ/ ሥነ-ሥርዓት ተጀመረ

እሑድ መስከረም 25, 2018 205

የኢሬቻ ሆረ ሀርሰዴ ‘የኢሬፈና’ /ምስጋና የማቅረብ/ ሥነ-ሥርዓት በአባገዳዎች ምርቃት በቢሾፍቱ ከተማ መልካ ሀርሰዴ መከናወን ጀምሯል።
አባገዳዎቹ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በቅደም ተከተል የምርቃት ሥነ-ሥርዓቱን ያከናውነዋል።
እናቶች እና አባቶች፣ ቄሮ እና ቀሬዎች ለምለም ሳር እና አደይ አበባ ይዘው “መሬ ሆ…!” እያሉ በታላቅ እልልታ እና ዝማሬ ምስጋና አቅርበዋል።
ሁሉም የበዓሉ ተሳታፊዎች “ሆ ያ መሬ ሆ …” እያሉ ጭጋጉ መገፈፉን፣ ፈጣሪያቸው ምሕረት ማድረጉን እና ከዘመን ዘመን ማሸጋገሩን አብስረዋል።
ኢሬቻ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ከጥንት ቅድመ አያቶቹ ጀምሮ ሕዝቡ ለፈጣሪ ምስጋና የሚያቀርብበት እና ሰላም የሚያጠናክርበት፣ ይቅርታ እና እርቅ የሚፈፀምበት በዓል ነው።