Search

የኢቲቪ ፓርላማ ቻናል ህብረተሰቡ በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ተሳትፎ እንዲያደርግ ያስችላል፡- አፈ ጉባዔ ፋንታየ ከበደ

እሑድ መስከረም 25, 2018 114

ኢቲቪ ፓርላማ ቻናል ሥርጭት መጀመሩ ህብረተሰቡ በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ተሳትፎ እንዲያደርግ እንደሚያስችለው የሲዳማ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ፋንታየ ከበደ ገለፁ።
አክለውም ፓርላማው ስለሚሠራው ሥራ ህብተሰቡ ሙሉ መረጃ እንዲኖረው ያግዛል ሲሉ ተናግረዋል።
ቻናሉ የክልል ምክርቤቶችን የሥራ እንቅስቃሴ ጭምር በተለያየ መልኩ ሽፋን የሚሰጥ በመሆኑ፣ ምክር ቤቶች የልምድ ልውውጥ ጭምር እንዲያደርጉ የሚያስችል ነው ብለዋል።
የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ከኢቲቪ የፓርላማ ቻናል ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን የገለፁት አፈ ጉባዔዋ፤ ሌሎች ክልሎችም ይህንን እድል መጠቀም ይኖርባቸዋል ብለዋል።
ምክር ቤቶች ለሀገር እድገት ወሳኝ የሆኑ ፓሊሲዎችና ሕጎች የሚፀድቁባቸው፣ ብሎም አስፈፃሚው አካል የፈፀማቸው ሥራዎች የሚገመገሙባቸው መድረኮች መሆናቸውን ገልጸዋል።
በመሆኑም ህብረተሰቡ በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ተሳትፎ እንዲያደርግ ቻናሉ ጉልህ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ነው ያሉት።
በፈቃደአብ አለማየሁ