ኢትዮጵያ ዘመናትን የተሻገረ የፓርላሜንታሪ ሥርዓትን ስትከተለ ኖራለች የሚሉት የአ/አ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ቡዜና አልቃድር፤ አሁን ያለው የኢፌዴሪ ፓርላሜንታሪ ሥርዓት ግን ብዙ መሻሻሎችና ለውጦች የሚታዩበት ነው በማለት ያስረዳሉ።
የኢቲቪ ፓርላማ ቻናል ሥራ መጀመር በርካታ በረከቶችን ይዞ ይመጣል የሚሉት አፈ ጉባኤዋ፥ ከቋንቋና ከተደራሽነት አንፃር ቀዳሚ እና ብዙዎችን ያስተሳሰረ ጣቢያ መሆኑን አስታውሰው፤ ሕዝቡ የምክር ቤት ስብሰባዎችን በቀጥታ መመልከት ማስቻሉ ትልቅ ዕድል መሆኑን ጠቁመዋል።
በፌዴራል፣ በክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ደረጃ ያሉ ምክር ቤቶች ተልዕኳቸው ተመሳሳይ ነው ያሉ ሲሆን፤ ሁሉም የሕዝቡን ተሳትፎ ይፈልጋሉ ለዚህም ኢቢሲ የሚጀምረው የኢቲቪ ፓርላማ ቻናል ሚና ከፍ ያለ ይሆናል ሲሉም ነው የገለጹት።
አክለውም የኢቲቪ የፓርላማ ቻናል በመከፈቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው፤ ሕዝቡ በቻናሉ የሚተላለፉ ውይይቶችንና ክርክሮችን በመከታተል ሀሳቡን እንዲሰጥ ጋብዘዋል።
በአሸናፊ ደምሴ