ኢሬቻ ዓለም አቀፍ ትኩረትን እየሳበ መጥቷል። በክብረ በዓሉ ላይ የሚሳተፉ የውጭ ሀገራት ዜጎችም ሆነ መገናኛ ብዙሃን እየተበራከቱም ነው።
ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችም ትኩረታቸውን በዚህ ታላቅ ክብረ በዓል ላይ አድርገው ውለዋል።
ከእነዚህም መካከል አሶሼትድ ፕሬስ የዘንድሮውን የኢሬቻ በዓል በተመለከተ 'በሺዎች የሚቆጠሩ ታዳሚዎች ያከበሩት የኢትዮጵያ የምስጋና ፌስቲቫል'' ሲል ዘግቧል።
በዓሉንም ሰላም እና አብሮነት የሚሰበክበት ነው ሲል ገልፆታል፡፡

ኢንዲፔንደንት በበኩሉ በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ በሺዎች የሚቆጠሩ ታዳሚዎች የሚሰበሰቡበት እና በየዓመቱ የሚከበረው የምስጋና ፌስቲቫል ሲል ስለ ኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ ክብረ በዓል አስነብቧል፡፡
በተጨማሪም ዋሺንግተን ፖስት፣ ዘ ካናዲያን ፕረስ፣ ቲ አር ቲ አፍሪካ እና ሌሎችም በድምቀት የተከበረውን የኢሬቻ ክብረ በዓልን የተመለከቱ ዘገባዎችን አውጥተዋል።
የዘንድሮዉ የሆረ ፊንፊኔ እና የሆረ ሃርሰዴ የኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መንገድ በስኬት ተከብሮ ተጠናቋል።