Search

በዩናይትድ ኪንግደም የኤሌክትሪክ መኪናዎች ፍላጎት አይሏል

እሑድ መስከረም 25, 2018 34

የዩናይትድ ኪንግደም የመስከረም ወር የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ከፍተኛ ሆኗል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
በዚሁ ወር ብቻ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪናዎች ሽያጭ 72 ሺ 779 መድረሱ ተገልጿል።
ይህ የመስከረም ወር ሽያጭ እ.አ.አ. ከ2020 ጀምሮ የተሻለው አፈፃፀም የታየበት ሆኗል።
በመስከረም ወር ከተመዘገቡት አዳዲስ የመኪና ግዢ ምዝገባዎች ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ መሆኑም ተመላክቷል።
በዩናይትድ ኪንግድም ዜጎች የተመረጡ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን እንዲገዙ ማበረታቻ ተደርጓል።
 
በሴራን ታደሰ