የኖርዌይ የኖቤል ኮሚቴ የ2025ቱን የዓለም የሰላም ኖቤል ሽልማት ለቬንዙዌላዊቷ ፖለቲከኛ ማሪያ ኮሪና ማቻዶ ሰጥቷል።
ፖለቲከኛዋ የዓለም የሰላም ኖቤል አሸናፊ የሆኑት በሀገራቸው የዴሞክራሲ ሥርዓት እንዲሰፍን ባደረጉት ብርቱ ጥረት መሆኑን ኮሚቴው ገልጿል።
ማሪያ ኮሪና ማቻዶ በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሂደት በአሳዩት አመራር እና ለሰላማዊ ትግል ቅድሚያ በመስጠታቸው በቬንዙዌላ እና በተለያዩ የዓለም ሀገራት በርካታ ተከታዮችን ማፍራትም ችለዋል፡፡
ፖለቲከኛዋ በሀገራቸው ቬንዙዌላ የዴሞክራሲ ንቅናቄን በመምራት ለሌሎች ላቲን አሜሪካውያን ምሳሌ የሚሆኑ ናቸው ሲልም የኖቤል ኮሚቴ ገልጿቸዋል።
በሃብተሚካኤል ክፍሉ