Search

የመድኃኒት ቁጥጥር ሥርዓትን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር ተችሏል፡- የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን

ዓርብ መስከረም 30, 2018 132

በኢትዮጵያ የመድኃኒት ቁጥጥር ሥርዓትን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር መቻሉን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሔራን ገርባ ተናግረዋል።
ዳይሬክተሯ ይህን የተናገሩት፤ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱና ተጠሪ ተቋማት በሶማሊ ክልል ጅግጅጋ ከተማ እያካሄዱ በሚገኘው ዓመታዊ የግምገማ መድረክ ነው።
ኢትዮጵያ በመድኃኒት ቁጥጥር ከዓለም ጤና ድርጅት 3ኛ ደረጃ (ማቹሪቲ ሌቭል-3) የብቃት ማረጋገጫን ማግኘት መቻሏ ለዚህ ትልቁ ማሳያ መሆኑን ያነሱት ዳይሬክተሯ፤ ለቀጣይ ስኬት በመፍጠርና መፍጠን መሄድ ያስፈልጋል ነው ያሉት።
በተለይ በመድኃኒት ቁጥጥር 4ኛ ደረጃ (ማቹሪቲ ሌቭል-4) ላይ ለመድረስ የሚድገውን ጥረት በማፋጠን፣ የኢትዮጵያን የማንሰራራት ዘመን ለማስቀጠል በቅርጠኝነት እንደሚሰራም ገልጸዋል።
 
በቴዎድሮስ ታደሰ