Search

ዛሬ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአዕምሮ ጤና ቀን እየተከበረ ነው

ዓርብ መስከረም 30, 2018 61

በዛሬው ዕለት ዓለም አቀፍ የአዕምሮ ጤና ቀን ስለአዕምሮ ጤና ግንዛቤ በማስጨበጥና የተለያዩ መርሐ ግብሮችን በማከናወን እየታሰበ ነው፡፡

የዘንድሮው የአዕምሮ ጤና ቀን "የአዕምሮ ጤና አገልግሎትን በድንገተኛ እና ከፍተኛ አደጋ ወቅት ተደራሽ እናድርግ" በሚል መሪ ቃል እየታሰበ የሚገኘው። 

ዓለም አቀፍ የአዕምሮ ጤና ቀን በየዓመቱ እ.ኤ.አ ጥቅምት 10 የሚከበር ሲሆን፤ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከበረዉም በ1992 ነበር።

የዓለም የአዕምሮ ጤና ፌዴሬሽን ቀኑ እንዲከበር የሐሳብ አመንጪ ሲሆን በስሩም ከ150 በላይ ሃገራትን በአባልነት ይዟል።

ዓለም አቀፍ የአዕምሮ ጤና ቀን መከበር ከአዕምሮ ጤና ጋር በተያያዘ በማኅበረሰቡ ዘንድ ያለውን ግንዛቤ ለማሳደግ እንደሚረዳ ይገለፃል።

የአዕምሮ ጤና ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተከበረ ሲሆን ቀኑ ስለአዕምሮ ጤና ግንዛቤ በማስጨበጥና የተለያዩ መርሐ ግብሮችን በማከናወን በተለያዩ ሀገራት እየተከበረ ነዉ።

ቀኑ በኢትዮጵያም በጤና ሚኒስቴር እና በተለያዩ የጤና ተቋማት ተከብሮ ዉሏል።

ዕለቱ በጤና ሚኒስትር በተከበረበት ወቅትም የአዕምሮ ጤና ችግር በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ተገልጿል፡፡

ከሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ አደጋዎች ጋር በተገናኘ የአዕምሮ ጤና ችግር እየጨመረ መምጣቱንም ነው የተገለፀው።

በአማኑኤል የአዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በድንገተኛ አደጋዎችና ሰብዓዊ ቀውስ ወቅት የሚከሰት የአዕምሮ ሕክምና አገልግሎት ያለበት ደረጃና ያሉ ክፍተቶች ላይም ውይይት ተደርጓል።

የዓለም የአዕምሮ ጤና ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ33ኛ ጊዜ፤ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ12ኛ ጊዜ ነው እየተከበረ የሚገኘው።

በቢታንያ ሲሳይ

#ebc #ebcdotstream #Ethiopia #world #Mental_Health_Day