Search

ከ4000 በላይ ተሳታፊዎች የሚታደሙበት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባዔ

ቅዳሜ ጥቅምት 01, 2018 62

ኢቢሲ በዳጉ ዝግጅቱ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እስካሁን የፈፀመውን ሥራ እንዲሁም ቀጣይ ተግባራትን በሚመለከት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬን (ዶ/ር) በስቱዲዮ ጋብዞ አነጋግሯል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር 3 ዋና ዋና ዓላማዎችን ይዞ የተነሳ መሆኑን የጠቀሱት ዶ/ር ዮናስ፤ እነዚህም በሀገሪቱ ሀገራዊ መግባባት እንዲሰፍን፣ በሕዝብ እና በመንግሥት እንዲሁም በህዝብ ለህዝብ መካከል መግባባት እንዲፈጠር፣ እንዲሁም ምክክርን የፖለቲካ ባሕል ማድረግ መሆናቸውን ዘርዝረዋል።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የተሰበሰቡ አጀንዳዎችን በማደራጀት፣ ለኢትዮጵያ ችግሮች መሠረታዊ የሆኑ ምክንያቶችን በመለየት፣ በቀጣይ የሀገራዊ ምክክር ጉባዔ ያካሂዳል።

በጉባዔው በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚወከሉ ከ4000 በላይ ተሳታፊዎች በተለዩ አጀንዳዎች ላይ ከተወያዩ በኋላ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውሳኔ ሀሳብ እንደሚቀርብ ነው ኮሚሽነሩ የገለጹት።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ እስካሁን በ11 ክልሎች እና 2 የከተማ አስተዳደሮች አጀንዳ የማሰባሰብ ሥራ አከናውኗል።

በምክክሩ በሀገር ቤት ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ባሻገር ባህር ማዶ ያሉ ዜጎችም ተሳታፊ እንዲሆኑ መደረጉንም ነው ያነሱት።

በኢትዮጵያ የኃይል አማራጭን ወደ ጎን በመተው በምክክር እና በንግግር ችግሮችን በመፍታት የሰለጠነ ኅብረተሰብን እንፍጠር በሚል ሀሳብ ሀገራዊ ምክክር ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።

በንፍታሌም እንግዳወርቅ

#ebcdotstream #nationaldialogue #ሀገራዊምክክር