Search

ሰንደቅ ዓላማ የማንነታችን እና የኅብረ-ብሔራዊ አንድነታችን መገለጫ ነው

ቅዳሜ ጥቅምት 01, 2018 65

18ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀንን ምክንያት በማድረግ በጋምቤላ ክልል የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

በፓናል ውይይቱ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ መሰረት ማቲዎስ፥ ሰንደቅ ዓላማ የማንነታችን እና የኅብረ-ብሔራዊ አንድነታችን መገለጫ ነው ብለዋል።

የሰንደቅ ዓላማ ቀን፥ ለሀገር ሉዓላዊነት፣ ለነፃነት እና ለሰንደቅ ዓላማ ክብር ተገቢውን እውቅና በመስጠት ኅብረ-ብሔራዊ አንድነትን ለማፅናት ታስቦ የሚከበር መሆኑን ጠቅሰዋል።

ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀንን ስናከብር ሰላማችንን በማስጠበቅ እንዲሁም ደማቅ ድሎቻችንን አጠናክረን በማስቀጠል ሊሆን ይገባልም ብለዋል።

ቀደምት ጀግኖች ኢትዮጵያውያን በክብር ያስረከቡንን ሰንደቅ ዓላማ አስጠብቆ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ከዜጎች ትልቅ ኃላፊነት ይጠበቃል ሲሉም አሳስበዋል።

የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ኩዊች ዊው፥ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በድል ባጠናቀቅንበት ማግስት መከበሩ የዘንድሮውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የጋምቤላ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አሺኔ አስቲን በበኩላቸው፥ በየተሰማራንበት መስክ ኅብረ-ብሔራዊ አንድነታችንን ለማጎልበት የሚያስችሉ ተግባራትን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል።

18ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችን እና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ!” በሚል መሪ ሀሳብ ከነገ በስቲያ ይከበራል።

በሚፍታህ አብዱልቃድር

#ebcdotstream #Ethiopia #nationalflagday