የአፍሪካውያን ኩራት የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የጋራ ተጠቃሚነትን መርህ አድርጎ የተገነባ መሆኑን ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ለዓለም አሳውቃለች።
በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ተደራዳሪ የሆኑት ኢንጂነር ጌዲዮን አስፋው፥ ከግድቡ ጋር በተያያዘ በርካታ የተሳሳቱ አስተያየቶች ሲሰነዘሩ እንደነበር አንስተው፤ ፍትሐዊ የጋራ ተጠቃሚነት የኢትዮጵያ የማይናወጥ አቋም መሆኑን ገልጸዋል።
ከሕዳሴ ትሩፋቶች አንዱ ከኢትዮጵያውያን አልፎ በአፍሪካውያን ዘንድ የፈጠረው የይቻላል እና የትብብር መንፈስ ነው ብለዋል።
የኪንግስ ኦፍ ዓባይ ሚዲያ ባለቤት የሆኑት ኡስታዝ ጀማል በሽር በበኩላቸው፥ በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ የተሳሳተ ትርክትን የፈጠሩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች እንደነበሩ አንስተዋል።
ኢትዮጵያውያን ግን በዚህ ተስፋ ሳይቆርጡ የፕሮጀክቱን ትክክለኛ ዓላማ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በማስረዳት እና በተባበረ ክንድ ለስኬት በቅተዋል ብለዋል።
የኢትዮጵያ አቋም በጋራ እንጠቀም የሚል በመሆኑ የታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራትም ይህንኑ ሃሳብ በአግባቡ ሊረዱ እንደሚገባም ገልፀዋል።
በሜሮን ንብረት