Search

ሞዴል የገጠር መንደሮች የምግብ ሉኣላዊነትን ለማረጋገጥ ወሳኝ ናቸው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ቅዳሜ ጥቅምት 01, 2018 55

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፌዴራል እና ክልል አመራሮች ጋር የገጠር ኮሪደር ሥራዎች ላይ አጭር ውይይት አድርገዋል።
በውይይታቸውም ሞዴል የገጠር መንደሮች የአርሶ አደሩን ሕይወት መቀየር ከቻሉ ኢትዮጵያ የምግብ ሉኣላዊነትን ማረጋገጥ የማትችልበት ምክንያት አይኖርም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የመቀንጨር ችግር አለ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በሞዴል የገጠር መንደሮች አማካኝነት ከጓሮ በቂ ፍራፍሬ፣ ፕሮቲን እና የተመጣጠነ ምግብ የሚሰጥ ምርት ካለ የሚራብ አርሶ አደር አይኖርም ሲሉ ተናግረዋል።
 
በአካባቢው ከሚገኙ ግብዓቶች የተሻለ መኖሪያ ቤት በመገንባት የአርሶ አደሩን ሕይወት ተቀይሮ ማየት ከተቻለ በሀገር አቀፍ ደረጃ ትልቅ ለውጥ ማምጣት ይቻላል ብለዋል።
የተጀመረው ሥራ በጣም አስደናቂ መሆኑን አንስተዉ፤ ይህንን ሥራ እንዴት ማስፋት እንችላለን የሚለው ጉዳይ ቁርጠኝነት ይፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።
ይሄን ማስፋት ከተቻለ ኢትዮጵያ ውስጥ የምናስበውን ለውጥ ለማምጣት ከፍተኛ እግዛ ያደርጋል ብለዋል።
 
በቢታኒያ ሲሳይ