Search

ወደተሟላ ብልጽግና የሚወስድ አይን ገላጭ ሥራ ተሰርቷል - አምባሳደር ሬድዋን ሁኔን

ቅዳሜ ጥቅምት 01, 2018 38

ሞዴል የገጠር መንደሮች ግንባታ ወደተሟላ ብልጽግና የሚወስድ አይን ገላጭ ሥራ ነው ሲሉ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ተናግረዋል።
ሞዴል የገጠር መንደር ሰዎችን በአንድ ቦታ ያሰባሰበ በመሆኑ ለኩታ ገጠም ግብርና እና ለመሰረተ ልማት ግንባታም አመቺ መሆኑን ነው ያመላከቱት።
በዘመናዊ የገጠር መንደሮቹ እናቶች ከማገዶ ጭስ ርቀው በዘመናዊ መንገድ እያበሰሉ ጤናቸውን ጠብቀው በንፅህና መኖር ይችላሉ ሲሉም ገልፀዋል።
የተሟላ ብልጽግና የሚባለውን ሃሳብ በሞዴል የገጠር መንደሮች አማካኝነት ማየት ተችሏል ያሉት አቶ ሬድዋን፤ አቅም ያላቸው አርሶ አደሮች ደግሞ በራሳቸው ዘመናዊ አኗኗርን እንዲመሰርቱ ማገዝ ያስፈልጋል ብለዋል።
አደጉ በሚባሉ ሀገሮች የተሻለው ሰው ከከተማ ወጣ ብሎ ዘመናዊ ቤት ገንብቶ ይኖራል፤ ይህ ልምድ በእኛም ሀገር እንዲዳብር ሞዴል የገጠር መንደሮች አይነተኛ ሚና አላቸው ሲሉ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን አመላክተዋል።