Search

ከቀለም የተሻገረ በመስዋዕትነት የከበረ ሰንደቅ ዓላማ

እሑድ ጥቅምት 02, 2018 138

ሰንደቅ ዓላማ የአንድ ሀገር መለያ፣ የሀገር ፍቅር ማሳያና የህዝቦች ማንነት መገለጫ ነው።

ዜጎች ለሀገራቸው ያላቸውን ፍቅር በሰንደቅ ዓላማ ሲገልፁም ይስተዋላል።

የማህበረሰብ አንቂው አቶ መሐመድ ካሳ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ሰንደቅ ዓላማ  የሀገርን መልክ እና ገፅ መመልከቻ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ብዙ ትርጓሜ ያለው እና ከፍተኛ መስዋዕትነት የተከፈለበት ስለመሆኑም አመልክተዋል።

በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ኢትዮጵያን የነፃነት ቀንዲል በማድረግ ሰንደቅ ዓላማቸውን  ተመሳሳይ ማድረጋቸውን አንስተዋል።

ይህ የኩራት እና የማንነታችን ዓርማ በመላው ዓለም በድል የምንታወቅበት መጠሪያችን ነው ሲሉም ገልጸዋል።

ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውን በሚገባ ስለ ሰንደቅ ዓላማ ሥነ-ስርዓት እና ስለ ሀገር ፍቅር ሊያስተምሩ እንደሚገባም ተናግረዋል።

በሜሮን ንብረት

#ebc #ebcdotstream #Ethiopia #National_flag_day