Search

ሰንደቅ ዓላማን በተመለከተ የተከለከሉ ተግባራት ምንድን ናቸው?

እሑድ ጥቅምት 02, 2018 319

በኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት አንቀፅ 3 ከሰፈረው የሰንደቅ ዓላማ ድንጋጌ እንዲሁም በሰንደቅ ዓላማ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 863/2006 መሠረት ሰንደቅ ዓላማን በተመለከተ የተከለከሉ ተግባራት፦ 

👉🏽  ሰንደቅ ዓላማው በወጣበት ሰንደቅ (ምሰሶ ወይም ፖል) ላይ ማስታወቂያ መለጠፍ፣ ያለአግባብ ሌሎች ሰንደቅ ዓላማዎች ወይም አርማዎችን ጨምሮ ማውለብለብ ወይም መገልገል

👉🏽  ሰንደቅ ዓላማው ላይ ቃላትን መጻፍ፣ ሌሎች ምልክቶች ወይም አርማዎችን መጠቀም ወይም መገልገል

👉🏽  ሰንደቅ ዓላማውን በአዋጅ በተደነገገው መሠረት የተቀመጡ አርማውን ሳያካትቱ መጠቀም

👉🏽  ሰንደቅ ዓላማው በሚሰቀልበት እና በሚወርድበት ጊዜ ተገቢውን ክብር አለመስጠት

👉🏽  በስብሰባ ወይም በማናቸውም መሰል ክንውኖች ሰንደቅ ዓላማውን የጠረጴዛ ሽፋን አድርጎ መጠቀም

👉🏽  ሕዝብ በተሰበሰበበት ቦታ ሰንደቅ ዓላማውን በጽሑፍ ወይም በቃላት ወይም በድርጊት ወይም በሌላ በማናቸውም አኳኋን ማዋረድ ወይም ጉዳት እንዲደርስበት ማድረግ

👉🏽  የንደቅ ዓላማውን ቀለማት ቅደም ተከተል እንዲሁም የብሔራዊ  አርማውን መጠን ሳይጠብቁ ማዘጋጀት እና መገልገል

👉🏽  በሰንደቅ ዓላማው አዋጅ ከተጠቀሰው የማውረጃ ጊዜ በላይ (ከፀሐይ መጥለቅ በኋላ) ተሰቅሎ እንዲቆይ ማድረግ እና በሰዓቱ አለመስቀል

👉🏽  ሰንደቅ ዓላማውን የሕንፃ ወይም የሌሎች ቁሳቁሶች መሸፈኛ ማድረግ 

👉🏽  ሰንደቅ ዓላማውን በማንኛውም ንግድ ማስታወቂያነት መጠቀም ዋና ዋና የተከለከሉ ተግባራት ናቸው። 

#EBC #ebcdotstream #EthiopianFlag #flag #nationalflagday