Search

ሰንደቅ ዓላማችን ጠላቶቻችን ሊሰብሩት የማይችሉት የሕብረ ብሔራዊነታችን ምሽግ ነው፡- አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ

ሰኞ ጥቅምት 03, 2018 42

ሰንደቅ ዓላማችን የውጭ እና እና የውስጥ ጠላቶቻችን ሊሰብሩት የማይችሉት የሕብረ ብሔራዊነታችን እና የሉዓላዊነታችን ምሽግ ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ገልጸዋል፡፡
18ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀ ሥላሴ፣ አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተከብሯል።
አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ በዚህ ወቅት፤ ሰንደቅ ዓላማችን የብዝኀነታችን እና የእኩልነታችን መገለጫችን ነው ብለዋል፡፡
የዘንድሮው የሰንደቅ ዓላማ ቀን የኢትዮጵያን የከፍታ ዘመን የሚያበስር ነው ያሉት አፈ ጉባዔው፤ ዛሬ ብሔራዊ አርበኝነታችንን የምንቀሰቅስበት ታላቅ እለት ነው ሲሉም አክለዋል፡፡
አፈ ጌባዔው፤ ሰንደቅ ዓላማችን ፈተናዎችን አብሮ በመሻገር አፍሪካዊ ተምሳሌት ሀገርን የመገንባት አቅማችንን የምናጎለብትበት ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ሰንደቅ ዓላማችን ዓለም አቀፍ ተፅዕኖ መፍጠሪያችን እና የማንሰራራት ጉዞ ዓርማችን ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
18ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን "ሰንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ" በሚል መሪ ሃሳብ በዛሬው ዕለት እየተከበረ ነው፡፡
በሜሮን ንብረት