"የትልቋ ሀገራችን ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ እና ይበልጥ እንዲከበር እንደ ብሔራዊ ሚዲያ ትልቅ ኃላፊነት አለብን ሲሉ የኢቢሲ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ቢኒያም ኤሮ ገለፁ።
የኢቢሲ ሠራተኞች የሰንደቅ ዓላማ ቀንን በተቋሙ ዋና ቢሮ ሰንደቅ ዓላማ በመስቀል አክብረዋል፡፡

ለኢትዮጵያውያን የኩራት ምንጭ ለሆነችው ለሰንደቅ ዓላማ ክብር እና ለኅብረ-ብሔራዊነት ኢቢሲ በኃላፊነት ተግቶ እንደሚሠራ አቶ ቢኒየም ኤሮ ተናግረዋል።
በጥቁር ሕዝቦች ታሪክ ትልቅ ቦታ ያላት ኢትዮጵያ ፤ ሰንደቋ እንዲከበርና ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ይበልጥ መሥራት እንደሚገባም አመላክተዋል።
ድኅነትን የማሸነፍ፣ እንደ ሀገር ከፍ የማለት፣ ወደ ሁለንተናዊ ብልፅግና የመጓዝ ጥረትን እና የተለያዩ የልማት ሥራዎች ዳር እንዲደርሱ ከኢቢሲ ብዙ መሥራት ይጠበቃል ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።
በላሉ ኢታላ