Search

"ሰንደቅ ዓላማችን ከአያት ቅድመአያቶቻችን የተላለፈ የደም ማሕተብ ነው"

ሰኞ ጥቅምት 03, 2018 28

ሰንደቅ ዓላማችን ከአያት ቅድመአያቶቻችን የተላለፈ የደም ማሕተባችን ነው ሲሉ የቀድሞ የሰራዊት አባል ሻለቃ ደምሴ ዮሃንስ ተናገሩ፡፡

የሰንደቅ ዓላማ ቀንን አስመልክቶ በኢቢሲ የዳጉ ፕሮግራም ላይ እንግዳ የነበሩት የቀድሞ የሰራዊት አባል ሻለቃ ደምሴ ዮሃንስ፤ ሰንደቅ ዓላማ በተለይ ለወታደር የተለየ ትርጉም እና ስሜት አለው ብለዋል፡፡

ሰንደቅ ዓላማችን ከአያት ቅድመአያቶቻችን ለትውልድ የተላለፈ የደም ማሕተባችን ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ መምህር አቶ ዘመዱ ደምስስ በበኩላቸው፤ ሰንደቅ ዓላማ አንድ ሀገር ከስሟ ቀጥሎ አብሯት የሚነሳ መለያዋ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ሰንደቅ ዓላማ አንድ ሀገር ከሌላው ሀገር በተለየ ይወክለኛል ብላ ያፀደቀችው መለያ ምልክቷ በመሆኑ በራሱ ለሀገሪቷ አምባሳደር በመሆን ከሌሎች የዓለም ሀገራት ጋር የሚያግባባ ቋንቋ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

የአንዲት ሀገር ሰንደቅ ዓላማ ከሀገር ታሪክ እኩል የመተረክ አቅም አለው ያሉት ምሁሩ፤ ሀገርን የሚወክሉ ትላልቅ ተቋማትም ሆኑ ግለሰቦች የሀገራቸውን ሰንደቅ በመያዝ በየትኛውም የዓለም ሀገራት እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ድንበር ተሻግሮ ሲገኝ ሀገርን ከመወከሉም ባሻገር ከዓድዋ ድል በኋላ ለሌሎችም መላ የጥቁር ሕዝቦች የፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄና የነፃነት ምልክት ሆኖ ማገልገሉንም አንስተዋል፡፡

በንፍታሌም እንግዳወርቅ

#EBC #ebcdotstream #ethiopianflag #flagday