የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስኬትና ዕድገት ማስቀጠል ያቻሉት የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው የ2025 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
የስታር አሊያንስ አባል የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በየዓመቱ አፍሪካን ከመላው ዓለም በማገናኘት በርካታ ሽልማቶችን አሸንፏል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በስካይትራክስ ለስምንተኛ ጊዜ የአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ የተባለ ሲሆን የአፍሪካ ምርጥ የቢዝነስ ክፍል፤ የአፍሪካ ምርጥ የኢኮኖሚ ክፍል እና በአፍሪካ ቢዝነስ ክፍል ምርጥ ምግብ አገልግሎት ሰጪ አየር መንገድ በመባልም ሽልማቶችን ማሸነፍ ችሏል፡፡
የአየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው የተቋሙን ስኬት እና ስትራቴጂካዊ ዕድገት በማስቀጠል ረገድ ባሳዩት የላቀ አፈፃፀም የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ተሸላሚ መሆን መቻላቸውን ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አየር መንገዱ አስተማማኝ የአየር ትራንስፖርት በመስጠት የሀገሪቱን ኢኮኖሚና፤ ቱሪዝም ለማሳደግ እንዲሁም ኢትዮጵያን የኮንፈረንስ እና የንግድ ማእከል በማድረግ የውጭ ምንዛሪ ግኝትን ለማሳደግ ተግቶ እየሰራ ይገኛል፡፡
የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ለትርፍ ያልተቋቋመው ኖቫ ኮኔክሽን የሚያዘጋጀው አመታዊ የእውቅና ሽልማት ሲሆን በአሜሪካና በአፍሪካ በሙያቸው ታላቅ ሥራ የሰሩ ግለሰቦችን ለማክበር የሚሰናዳ ነው።
በላሉ ኢታላ
#ebc #ebcdotstream #Ethiopia #EthiopianAirlines #award