Search

የባሕር በር ጥያቄ ብሔራዊ ሕልውናን የማስቀጠል ጉዳይ ነው

ማክሰኞ ጥቅምት 04, 2018 101

የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ግዛትን የማስፋፋት ጉዳይ ሳይሆን ሀገሪቱ ብሔራዊ ሕልውናዋን ለማረጋገጥ የምታደርገው ጥረት አካል መሆኑን የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር ጃፋር በድሩ ገለፁ።
የባሕር በር ጥያቄው የማንኛውንም ሀገር ሉዓላዊነት የማይጋፋ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፤ ይህ ፍትሐዊ ጥያቄ የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረገ መሆኑን አበክረው ተናግረዋል።
የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህር አንዱዓለም በጋሻው በበኩላቸው፤ የባሕር በር ከጂኦፖለቲክስ ባሻገር ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታችንን በእጥፍ ይጨምራል ብለዋል።
ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር አቅራቢያ ከሚገኙ ሃገራት መካከል አንዷ ሆና ሳለ፣ ወደብ አልባ ሀገር ተብላ ልትጠራ አይገባም ብለዋል የምጣኔ ሀብት መምህሩ።
ከዓለም ጋር ለመገናኘት የባሕር በር ወሳኝ መሳሪያ ነው የሚሉት ደግሞ የሚዛን ቴፕ ዩኒቨርሲቲ ዓለም አቀፍ ግንኙነት ክፍል ኃላፊው ረጋሳ ቤኛ (ዶ/ር) ናቸው፡፡
የባሕር በሩ ከፍታ ላይ ልናያት ምንፈልጋትን ኢትዮጵያን ለመስራት ጉልህ ሚና አለው ሲሉም ገልጸዋል።
ጥያቄው ዓለም አቀፍ ቅቡልና እንዲኖረው፣ ከዲፕሎማሲያዊ ሥራ ባለፈ በውጭም ሆነ በሀገር ውስጥ ያሉ ዜጎች በዚህ ጉዳይ ላይ ድርብ ኃላፊነት እንዳለባቸው ጠቁመዋል።
በሴራን ታደሰ