ዓለም አቀፉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን 44ኛው አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል።
ጉባኤውን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በጸሎተ ቡራኬ አስጀምረውታል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን በጥበብ በመምራት ለመጭው ትውልድ ማሻገር እንደሚያስፈልግም በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መዕልክታቸው ተናግረዋል።
በጉባኤው ላይ በቤተ ክርስቲያን እና ገዳማት ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮች ቀርበው የመፍትሔ ሐሳቦች ይሰጥባቸዋል የተባለ ሲሆን፤ ቤተ ክርስቲያኗ ያከናወነቻቸው ተግባራት ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ይገኛል።
በየዓመቱ በጥቅምት ወር በሚካሔደው በዚህ ጉባኤ ለቤተክርስቲያን አገልግሎት የሚጠቅሙ፣ ለመንፈሳዊ አስተዳደሯም የሚበጁ መሠረታዊ ጉዳዮች ይቀርባሉ።
በሚቀርቡት ሪፖርቶች ላይም ውይይት እና የልምድ ልውውጥ ተደርጎ የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ይሸለማሉ፤ ዝቅተኛ አገልግሎት ይዘው የመጡ ደግሞ ከጉባኤው ልምድ ቀስመው አገልግሎታቸውን እንዲያሻሽሉ ይመከራሉ ተብሏል።
በመሐሪ ዓለሙ
#EBC #ebcdotstream #EOTC #religion