የተለያዩ ሀገራት መሪዎች የተሳተፉበት በሴቶች ጉዳይ ላይ የሚመክር ዓለም አቀፍ የመሪዎች ጉባዔ በቤጂንግ፣ በቻይና ኮንቬንሽን ማዕከል ተካሂዷል።
በቻይናው ኘሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ በተከፈተው ዓለም አቀፍ ጉባዔ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሐመድን ጨምሮ የተለያዩ መሪዎች መልዕክት አስተላልፈዋል።
በኢትዮጵያ በኩል በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጐጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) የተመራ የልዑካን ቡድን በጉባዔው የተሳተፈ ሲሆን፤ ሚኒስትሯ ኢትዮጵያ የቤጂንግ+30 ቃል ኪዳንን በመፈጸም ረገድ ያከናወነቻቸውን ውጤታማ ሥራዎች አብራርተዋል።
ጉባዔው የሴቶች መብት ጥበቃን የበለጠ ለማጎልበት እንዲሁም ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ ትልቅ ዕድል የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህ ረገድ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና የቻይና መንግሥት እያደረጉት ያለውን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉም ሚኒስትሯ ጥሪ አቅርበዋል።
#ebcdotstream #womensrights #china #beijing