Search

ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ከሶሪያ ፕሬዝዳንት አህመድ አል ሻራ ጋር በሞስኮ ተወያዩ

ረቡዕ ጥቅምት 05, 2018 46

የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን እና የሶሪያ አረብ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት አህመድ አል ሻራ በክሬምሊን ውይይት አድርገዋል።

ሁለቱ ወገኖች በውይይታቸው በሀገራቱ መጻዒ የሁለትዮሽ ግንኙነት እና በሶሪያ የሚገኙ የሩሲያ ጦር ሠፈሮች ጉዳይ ላይ ትኩረት አድርገው መምከራቸው ተገልጿል፡፡

ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል ለረዥም ዘመናት የቆየ ወዳጅነትና ግንኙነት እንዳለ አንስተው፤ በአልሻራ የሚመሩት ኃይሎች በሶሪያ ድል መቀዳጀታቸው ለሀገሪቱና ለህዝቡ ትልቅ ስኬት መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ፕሬዝዳንት አህመድ አል ሻራ በበኩላቸው፤ አዲሱ የሶሪያ መንግሥት ከሩሲያ ጋር ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት ማደስ እንደሚፈልግ ተናግረዋል፡፡

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ፤ በዛሬው ዕለት በሁለቱ መሪዎች መካከል የተደረገው ውይይት ለሩሲያ እና ሶሪያ ግንኙነት ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን መጥቀሳቸውን ስፑቲንክ ዘግቧል።

#ebc #ebcdotstream #Russia #Syria