Search

በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ታሪካዊ መርሐ ግብር በይፋ ተጀመረ

ሰኞ ሐምሌ 27, 2018 44

በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል አዲስ ታሪክ የሚጻፍበት ሀገራዊ መርሐ ግብር በይፋ መጀመሩን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ አብሥረዋል።

ሚኒስትሯ መርሐ ግብሩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፣ መላው ኢትዮጵያውያን የተጎሳቀለችውን ምድር ለማዳን እና እንደተለመደው ታሪክ ለመሥራት በአንድነት መነሣታቸውን ገልጸዋል።

"ኢትዮጵያውያን ዝቅ ብለው ለመሬት አደራ ይሰጣሉ፤ ምድርም የተሰጣትን አደራ እጥፍ አድርጋ ትመልሳለች" በማለትም የሕዝቡን አኩሪ ባህል እና የምድሪቱን ፀጋ አወድሰዋል።

በመደመር መርሕ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል በአንድነት ወጥቶ ለቀጣዩ ትውልድ የሚተላለፍ ዐሻራውን እንዲያሳርፍና " ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሐሳብ ደማቅ ተሳትፎ እንዲያደርግ ሚኒስትሯ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

800 ሚሊዮን ችግኞች፣ በተግባር እና በሐሳብ አንድነት በመደመር ዕሳቤ እናሳካለንም ብለዋል።

ይህ ታሪካዊ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ከዚህ ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ በመላው ሀገራችን በሚገኙ ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍሎች የነቃ ተሳትፎ በደማቅ ሁኔታ የሚከናወን ይሆናል።

በለሚ ታደሰ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: