የፖለቲካ ተንታኝ እና የማህበረሰብ አንቂ የሆኑት አቶ አያና ፈይሳ ኢትዮጵያ ጀምሮ በመፈፀም ልምዷ የባሕር በር ጉዳይን ማሳካት እንደምትችል ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ የጎረቤት ሀገራትን ተጠቃሚነት ባረጋገጠ መልኩና በዲፕሎማስያዊ መንገድ የባሕር በር ጥያቄዋን በማቅረብ ትክክለኛ አቋሟን ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ማስረዳቷን የፓለቲካ ተንታኙ ጠቅሰዋል።
ሀገሪቱ ያላትን ዕምቅ ሀብት በመጠቀም የኢኮኖሚ ዕድገቷን ለማረጋገጥ በምታደርገው ጥረት የባሕር በር ጉዳይ የህልውና ጉዳይ ሆኖ እንደሚቀርብም ገልፀዋል።
እንደሀገር ኢትዮጵያ በውስጧ የሚነሱ ጥያቄዎች ቢኖሩም ጠንካራ ሆና የምትወጣበት ታሪክ ለመስራት ሕዝቧ አብሮ ሚቆምበት ቦታ ላይ በጋራ ሲቆም ውጤት እንደሚያመጣ የዓድዋ ድል እና የሕዳሴ ግድብ ማሳያ ናቸው ብለዋል።
ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት የህዳሴ ግድብ አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደሆነ ገልፀው፤ ጥረቱን ወደ ስኬት ለማምጣት ሀገሪቱ የምትከተላቸው ዲፕሎማሲያዊና ፖለቲካዊ መንገዶች ጉልህ ሚና እንዳለቸው ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት በምታደርገው ጥረት ሕዝቦቿ በጠንካራ አቋም አንድ ሆነው ከቆሙ የማይሳካበት አንዳችም ምክንያት የለም ብለዋል።
ሕዝብ ደጀን ያልሆነለት መንግስት ብቻውን ወሳኝ የሀገር ጉዳዮችን ማሳካት አይችልም ያሉት አቶ አያና፤ ህዝቡ ከማንነቱ፣ ከህልውናው እና ከነገ ተስፋው ጋር የተሳሰረውን የባህር በር ጉዳይ በትኩረት ሊመለከተው እንደሚገባ ተናግረዋል።
በሀገር ውስጥም ይሁን በውጪ ያሉ ዜጎች የኢትዮጵያን የባሕር በር ጥያቄ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ የማሳወቅ ስራን አጠናክረው መቀጠል እንደሚባቸውም አቶ አያና ገልፀዋል።
በሔለን ተስፋዬ
#EBC #ebcdotstream #Ethiopia #AccesstoSea