በኦሮሚያ ክልል የቦረና ዞን ዋና ከተማ የሆነችው ያቤሎ ህብረ-ብሔራዊ ቀለም የሚንፀባረቅባት የፍቅር ከተማ ናት፡፡
ያቤሎ ‘የሰላም ከተማ’፣ ‘የሰላም አምባሳደር‘ የሚሉ ቅጥያ ስያሜዎችንም አፍርታለች፡:
ከአዲስ አበባ 570 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ከተማዋ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦችን የያዘች ሲሆን ሁሉም ተከባብሮ በጋራ የሚኖርባት በመሆኗ ነው የተጠቀሱትን ቅጥያ ስያሜዎች ያገኘችው::
በያቤሎ የኦሮምኛ ቋንቋ በስፋት ቢነገርም ሌሎች ቋንቋዎችም ይነገርባታል::
በከተማዋ አብዛኛው ነዋሪ አርብቶ አደር ሲሆን ከሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች አንፃር ሞቃታማ የአየር ጠባይ አላት::
እድገቷ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ በርካታ ጎብኚዎችን ብሎም ኢንቨስተሮችን የምትስብ ከተማ መሆኗን ኢቢሲ የቅኝት መሰናዶውን ሲያሰናዳ ለመመልከት ችሏል፡፡
ከወራቶች በፊት በከተማው የተመረቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ማረፊያ አካባቢውን ለማስተዋወቅ እና ከሌሎች ከተሞች ጋር ያለውንን ትስስር ከፍ ለማድረግም አስችሏል::
በአፎምያ ክበበው
#ebc #ebcdotstream #Ethiopia #yabelo