ዓድዋ ታሪክን የወሰነ ማርሽ የተቀየረበት ዕለት ነው፤ የጥቁር ዘር ሁሉ የነፃነት ምልክትም ነው።
የዓድዋ ድል የተረጋገጠው ወረ ኢሉ ላይ እንደሆነ ይጠቀሳል። ወረ ኢሉ፣ ልዩነት ሳይገድባቸው ለጋራ ሀገር ተጋድሎ የመሪን ጥሪ ተቀብለው ኢትዮጵያወያኑ የተሰባሰቡበት ቦታ ነው።
ዓድዋ፣ ኩርፊያ ውስጥ የነበሩ ኃይሎች ሀገርን አስቀድመው በአንድ ምሽግ ወድቀው የዘመን ብዛት የማያወይበው ታሪክ የሠሩበትም ነው።
የዓድዋ፣ ድል እጅ ለእጅ ተያይዘን የወደቅንበት፤ በአንድነት የተጋመድንበት፤ በሰው ልጆች የነፃነት ተጋድሎ አዲስ ታሪክ የተመዘገበበት ዕለት ነው።
እናም የዓድዋ ድል የአንድ ቀን የጦርነት ውጤት ሳይሆን የአንድነት ውጤት ነው፤ ኩርፊያ ለሀገር መቆምን እንደማይገድብ ያየንበትም ነው።
ዛሬም ሀገር በመደመር እሳቤ የተፈጥሮ ሀብታም፣ የልማት ደሃ ሆና የቆየችበትን የቁጭት ታሪክ ለመቀየር ጥሪ አቅርባለች። ከኢትዮጵያውያንም ለዓድዋ ጥሪ የሰጡት ፈጣን ምላሽ ይጠበቃል።
የመደመር መንግሥት በአዳዲስ ዕይታ ኢትዮጵያን ወደ ብልፅግና መንገድ እየመራት ነው። ወደ ብልጽግና የሚደረገው ጉዞ መንገዱ የተደላደለ ይሆን ዘንድ ግን ሁሉም ትብብርን ሊያስቀድም ይገባዋል።
በእርግጥ የትውልዱን ጣጣ ያቃለለውን ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ያሳካው የመደመር ትውልድ የአባቶቹን ታሪክ ደግሟል።
ሐሳቡ መደመር፤ ሒሳቡ መፍጠን፣ መፍጠር እና መዝለል፤ ፍፃሜው ደግሞ ከበለፀጉ ሀገራት ተርታ የመሰለፍ ጉዞ ተጀምሯል።
በዚህም ሀገር እና ሕዝብን በማሰናሰል የራስን መጪ ዘመን በራስ መጽሐፍ ይጠበቃል።
በታሪከ የሚታወስ በትውልድ የሚነግር የጉስቁልና ዘመን ማክተሚያ የሚርጋገጥባቸው የአዳዲስ ዕይታ ውጤቶችን ማየት ተጀምሯል።
‘አይሆንልንም’ የሚል አዚምን ከሰበረው የሕዳሴ ግድብ ስኬት በኋላ ጋዝን በማውጣት ተፈጥሮ ለኢትዮጵያ ያደላትን ሀብትም መጠቀም ጀምረናል።
ኢትዮጵያ ሕልሞቿን ወደ ተግባር፣ ርዕይዋን ወደ ድል እየቀየረች ያለች ሀገር ናት። የትላልቅ ወንዞች ሀገር መሆን ብቻ ሳይሆን በትላልቅ ወንዞቿ ታሪክ ወደ መሥራት ተሸጋግራለች። የገዘፈ ታሪኳን የሚመጥን ትልቅ ሀገር ለመሆን የጀመረችው ጉዞ በዓድዋ እና በሕዳሴ የታየውን ትብብር ይፈልጋል።
የመደመር ትውልድ ለሺህ ዓመታት ጥያቄዎች መልስ በመስጠት የሀገርን የድህነት ስም ለመቀልበስ በመትጋት ላይ ነው።
የመጪው ዘመን ከተሞች እየተገነቡ ነው። በገጠርም ተበታትኖ የመኖር ባህልን የሚያሰቀሩ እና ፅዱ መንደሮች እየተገነቡ ነው።
የምንገዛው ብዙ፣ የምንሸጠው ጥቂት ሆኖ ለዘመናት የቀጠለውን ችግር የማስተካከል ሥራ ተጀምራል።
ኢትዮጵያ ዐይን የሚመገባውን አብዝታ ልትሰጥ የምትችል ናት። ይህን ሀብታችንን መግልጥ ተጀምሯል።
ከወደብ አልባነት ወደ ባሕር በር ባለቤትነት የሚደረግ ጉዞን ማሳካት የመደመር መንግሥት አሳካቸዋለሁ ከሚላቸው ቀዳሚ ግቦች አንዱ ነው።
ይህን የሀገር ሕልም ከግብ ለማድረስ ትናንት የምንታወቅበት፤ ዛሬ የምንተገብረው፤ ነገም የምናስቀጥለው ወርቃማው ኅብረታችን እና አንድነታችን በእጅጉ ያስፈልጉናል።
የቀደሙት ትውልዶች ወረ ኢሉ ላይ በአንድነት ተሰባስበው ኢትዮጵያን የዓድዋ ንግሥት አድርገዋታል።
የዛሬው የመደመር ትውልድ ደግሞ በዓድዋ የተገኘውን ነፃነት የኢትዮጵያን የድህነት ስም በመቀየር የተሟላ የድል ባለቤት ለመሆን እየተጋ ነው።
ኢትዮጵያ በዓለም አደባባይ ከፍ ብላ ትታይ ዘንድ የዓድዋ ድል አሻራ አኑሯል።
ብዝኃነት አንድ ከመሆን፤ አንድ መሆንም ከብዝኃነት ሳይጣረስ በወንድማማችነት የዘመቱ ኢትዮጵያውያን የዓድዋ ድልን አስገኝተዋል።
ዛሬ የዓድዋ ድል ተገቢውን ክብር እንዲሰጠው ሁሉም በአንድ ቃል ሀገሩን የማበልፀግ የመደመር መንግሥት ጥሪን ሊከተል ይገባል።
በዓድዋ ድል ለአፍሪካ የነፃነት መንገድን እንዳሳየን ሁሉ ዛሬም አፍሪካ በምግብ ራሷን እንድትችል ትዕምርት የሆኑ ሥራዎች ከመደመር ትውልድ ይጠበቃሉ።
የዓድዋ ድል ያስገኙልንን አባቶች ውለታ የምንከፍለው መጪውን የከፍታ ዘመን እውን በማድረግ ነው።
በንብረቴ ተሆነ
#EBC #ebcdotstream #Adwa #GERD #unity #medemer