Search

በክልሉ የተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎች ውጤት እየታየባቸው ነው - ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

ሓሙስ ጥቅምት 13, 2018 42

ክልሉን የሰላም ተምሳሌት ለማድረግ የተለያዩ የሪፎርም ሥራዎች መከናወናቸውን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለፁ።
ይህንን ያሉት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ለመጀመሪያ ዙር ያሰለጠናቸውን ምልምል ኮንስታብል ፖሊሶችን በምዕራብ አባያ ፖሊስ ማሰልጠኛ ማዕከል ባስመረቀበት ወቅት ነው።
ርዕሰ መስተዳድሩ፣ ተመራቂዎች ሕዝቡን በሰብዓዊነት ለማገልገል መዘጋጀት እንደሚኖርባቸው ጠቁመዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፍስሃ ጋረደው በበኩላቸው፣ በኮሚሽኑ ተግባራዊ የተደረገው የሪፎርም ሥራ ተቋሙን በሰለጠነ የሰው ኃይል ለማደራጀት ማስቻሉን ገልጸዋል።
የተቋሙን የመፈጸም አቅም ለማሳደግ በሰው ኃይል ልማት የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አብራርተዋል።
ተመራቂዎች በበኩላቸው፣ ባገኙት ዕውቀት ማኅበረሰቡን ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በመርሃግብሩ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ወገኔ ብዙነህን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን ርዕሰ መስተዳድሩ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተመራቂዎች የማበረታቻ ሽልማት ሰጥተዋል።
 
በተመስገን ተስፋዬ