Search

ኢትዮጵያ ልዩ ጥንካሬ እና የእድገት ፍጥነት ያሳየችበት አፈፃፀም

ሓሙስ ጥቅምት 13, 2018 72

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የመቶ ቀን እቅድ ግምገማ አካል ሆኖ የቀረበው ሪፖርት የዓለምን የኢኮኖሚ አዝማሚያ፣ የኢትዮጵያን ማክሮ ኢኮኖሚ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም እንዲሁም የእድገት አዝማሚያን እና አጠቃላይ ምልከታን አካትቷል።
በዚህም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ፣ በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ አዝማሚያዎች አውድ ውስጥ፣ ልዩ ጥንካሬ እና የእድገት ፍጥነት ማሳየቱ ተገልጿል።
በ2017 የበጀት ዓመት የኢትዮጵያ አጠቃላይ የኢኮኖሚ አፈጻጸም በጥንካሬው በመቀጠል 9.2 በመቶ ዓመታዊ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) እድገት ማሳየቱ ተመላክቷል።
በመንግሥት እየተካሄዱ ባሉ የተለያዩ የልማት ሥራዎች እና በአዲስ ኢንቨስትመንቶች በመደገፍ በ2018 ዓመተ ምህረት ኢኮኖሚው በ10.2 በመቶ እንደሚያድግ ይጠበቃል ተብሏል።
እንደ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ያሉ ፕሮጀክቶች መጠናቀቅ ብሎም እንደ የማዳበሪያ ማምረቻ እና የተፈጥሮ ጋዝ ልማት ሥራ ጅማሮዎች የኢኮኖሚ እድገቱን የበለጠ እንደሚያነቃቁ ተገልጿል።
የውጭ ንግድ 2.5 ቢሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን ይህም እቅዱን እና የባለፈውን ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ አፈጻጸምን የበለጠ ሆኖ መታየቱን ተመላክቷል።
በአጠቃላይ፣ አፈጻጸሙ በሁሉም መስኮች የተሻለ ውጤትን የሚያሳይ ሲሆን፣ ይኽም ኢትዮጵያ ወደ ኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር ብሎም ዘላቂ እና አካታች የኢኮኖሚ እድገት የምታደርገውን ፈጣን ሂደት የሚያረጋግጥ መሆኑን ተገልጿል።