Search

ለኢኮኖሚ እድገቱ ወሳኝ ሚና እየተወጣ ያለው የኢንዱስትሪ ዘርፍ

ሓሙስ ጥቅምት 13, 2018 27

የመደመር መንግሥት ለኢንዱስትሪ ዘርፉ የተሻለ ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዚህ ቀደም መግለጻቸው ይታወሳል።
ባለፉት ሦስት ወራትም የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ዘርፍ በ13 በመቶ በማደግ አጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገቱን እየመራ መሆኑን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ገልፀዋል።
ሚኒስትሯ እንዳስታወቁት፤ ባለፈው ዓመት እና ዘንድሮ በመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት በጠቅላላ 132 አዳዲስ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ ገብተዋል።
ለግሉ ዘርፍ እና ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንዱስትሪዎች የሚደረገው የፋይናንስ ድጋፍ ከፍ ማለቱ በዘርፉ ላይ ትልቅ ለውጥ እያመጣ መሆኑን አመላክተዋል።
በተጨማሪም በፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ የላብራቶሪ የቁጥጥር ደረጃ (Maturity Level) ሦስት ላይ የደረሱ የዓለም ሀገራት 60 ሲሆኑ፤ በአፍሪካ ደግሞ 9 ሀገራት ብቻ መሆናቸውን ጠቁመው፤ ኢትዮጵያ ይህን ውጤት ያገኘች በአፍሪካ ቀንድ የመጀመሪያው ሀገር መሆኗንም አብራርተዋል።
አዳዲስ ወደ ሥራ የሚገቡ የኢንዱስትሪ እና የማዕድን ፕሮጀክቶችም ኢኮኖሚው ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸውም ሚኒስትሯ ገልጸዋል።
 
በቢታኒያ ሲሳይ