Search

የአዲሱ ትውልድ ዐርበኝነት

ዓርብ ጥቅምት 14, 2018 97

የዛሬው ትውልድ ዐርበኝነት የሚለካው የጦር መሣሪያ በማንሣት ሳይሆን ሀገሩን በዘላቂነት ለማልማት በሚያሳየው ጥረት እና ውጤት ነው።

ለኤፍ ኤም አዲስ 97.1 አስተያየታቸውን የሰጡት አባት ዐርበኞች፣ የአዲሱ ትውልድ ዐርበኝነት የዘመናዊቷን ኢትዮጵያን ደማቅ ታሪክ የሚጽፍ ነው ሲሉ ገልጸውታል።

ዘመናዊ የሆነች ኢትዮጵያን በመገንባቱ ረገድ መሣሪያው ትምህርት እና ልማት ነው የሚሉት የቀድሞ አባት ዐርበኞች፣ ከአሁን በኋላ ያለው ጦርነት የልማት ጦርነት ነው ሲሉም ገልጸዋል።

አዲሱ ትውልድ የትናንት ታሪክን የሚዘክር ብቻ ሳይሆን የልማት ዐርበኛ በመሆን እርሱም ለነገው ትውልድ የራሱን ዐሻራ ማሳረፍ እንደሚገባው ምክራቸውን ለግሰዋል።

በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ተረጂነትን እና ጥገኝነትን የሚጠየፍ እና የራሱን ዐሻራ በማሳረፍ ላይ የሚገኝ አዲስ ዐርበኛ ትውልድ እያፈራች ነው ይላሉ።

የአዲሱ ትውልድ የልማት ዐርበኝነት ከተገለጸባቸው መንገዶች መካከልም ኢትዮጵያ ላለፉት ሰባት ዓመታት የከወነችው የአረንጓዴ ዐሻራ ነው።

ከአዲስ አበባ ጀምሮ በተለያዩ ከተሞች እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት እና ዳግም ዓድዋ የሆነው ታላቁ የሕዳሴ ግድብም አንዱ መገለጫ ነው።

ሌሎች ታላላቅ ፕሮጀክቶች ተጀምረው መጠናቀቅ የቻሉበ በመሆኑም የአዲሱ ትውልድ የዐርበኝነት ሥራውን በማከናወን በልማት ጎዳና ላይ እንደሚገኝ ሕያው ምስክር ናቸው።

በንፍታሌም እንግዳወርቅ

#EBC #EBCdotstream #Ethiopia #Newgeneration #patriotism