Search

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ስምረት ፓርቲ የምሥረታ ጉባኤውን እያካሄደ ነው

ዓርብ ጥቅምት 14, 2018 104

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ስምረት (ስምረት) ፓርቲ ከፍተኛ የፓርቲው አመራሮች እና መሥራች አባላቱ በተገኙበት ዛሬ የመጀመሪያ ጉባዔውን እያካሄደ ይገኛል።

በጉባኤው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ፓርቲው ለትግራይ ሕዝብ ሁለንተናዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት በሚሆን መልኩ በአዲስ አስተሳሰብ የተዋቀረ መሆኑን ገልጸዋል። 

የብልፅግና ፓርቲን ወክለው የተገኙት አቶ መለስ ዓለም፣ አዳዲስ የፖለቲካ ፓርቲዎች በትብብር መሥራታቸው ኢትዮጵያ የጀመረችው አዲስ የፖለቲካ አካሄድ ማሳያ ነው ብለዋል። 

ስምረት ፓርቲም ለትግራይ ሕዝብ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ተሳትፎ አዲስ ሐሳብ ይዞ የመጣ ፓርቲ እንደመሆኑ ከብልፅግና ፓርቲ ጋር ያለው የፖለቲካ እና የአቋም ልዩነት እንዳለ ሆኖ ሀገራችን ለጀመረችው ጉዞ የሚኖረው አበርክቶ ግን የጎላ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

በዚሁ በፓርቲው የምሥረታ ጉባኤ ላይ የተገኙ አባላትም የትግራይ ሕዝብ በተለይም ወጣቱ ለውጥ እንደሚፈልግ ተናግረዋል። 

ትግራይ ከደረሰባት ውድመት ማገገም እና መልማት አለባት ያሉት አባላቱ፣ ለዚህ ደግሞ ጠመንጃን አማራጭ ካደረገ የኃይል አካሄድ በመውጣት ዘመኑን በዋጀ እና ውይይትን መሠረት ያደረገ አካሄድ ያስፈልጋል ብለዋል።

በዘሃራ መሐመድ 

#EBC #ebcdotstream #Simretpary #politics