Search

በሚቀጥሉት ወራት ለምርቃት ወረፋ የሚጠብቁ ግድቦች አሉ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ዓርብ ጥቅምት 14, 2018 43

ሥራቸው ተጠናቅቆ በሚቀጥሉት ወራት ሊመረቁ ወረፋ የሚጠብቁ ከትናንሽ እስከ ትላልቅ ግድቦች መኖራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ።

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ የመፍጠር እና መፍጠን አስፈላጊነት በደንብ እየታየ መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ በዚህ ሂደትም በርካታ ፕሮጀክቶች ተጠናቅቀው መመረቃቸውን አንስተዋል።

በመፍጠር እና በመፍጠን ካልሆነ ኢትዮጵያን መቀየር እንደማይቻል ግንዛቤ እየተፈጠረ እና በዚህ መንፈስ ወደ ሥራ እየተገባ መሆኑንም ተናግረዋል።

ግድብን ብቻ ብንመለከት ሕዳሴን እንዲሁም ወልመልን አስመርቀናል፤ ሥራቸው ተጠናቅቆ ለምረቃ የተዘጋጁ ተጨማሪ ግድቦችም አሉ ብለዋል።

"እንደዚህ ያለው አውድ ውስጥ ያስገባን መፍጠር እና መፍጠን ነው" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በየቦታው ተመሳሳይ አሠራሮች እየተለመዱ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በመንግሥት እና ማኅበረሰብ ትብብር መሥራትም ባህል እየሆነ መምጣቱን ጠቅሰው፣ በዚህም ትምህርት ቤቶችን ማስፋፋትን ጨምሮ በርካታ ፕሮጀክቶች መሠራታቸውን ተናግረዋል።

በለሚ ታደሰ

#EBC #EBCdotstream #PMOEthiopia #AbiyAhmedAli #projects