የኢትዮጵያ የወደፊት ጉዞን ማንም ሊያስቆመው የማይችልበት ደረጃ ላይ እየደረሰ ነው ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ገለጹ።
ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ይህን ያሉት “የሚኒስትሮች ምክር ቤት ምልከታ በኮይሻ” የውይይት መድረክ ላይ ነው።
አንዳንዶች ትናንትን በማሰብ ብቻ ካለእኛ ሥራ አይሠራም፣ ሀገር ለማደግ የግድ የእኛ አስተዋጽኦ ያስፈልጋታል ብለው ያስባሉ፤ ከዚህ ሀሳብ በመነሳትም የሚሠራ ሰው ሲገኝ ደግሞ ሥራውን ለማስተጓጎል ይጥራሉ ብለዋል።
እንዲህ ያሉ ሰዎች በሚያድግ ሀገር ያሉ ዜጎች እና አመራሮች ሥራቸው ላይ ብቻ የሚያተኩሩ መሆናቸውን ይረሱታል ብለዋል።
በዚህ የ100 ቀን ግምገማ ላይ የታዘብኩትም ይህንኑ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ ዜጎች ለማደግ ጠንክረው ሀገራቸውን ለማሳደግ እየተጉ ነው፤ አመራሩም በቁርጠኝነት ሚናውን እየተወጣ ነው ብለዋል።
አንዳንዶች ደግሞ ትናንት ላይ ቆመው የዛሬ ታሪክ እያመለጣቸው ነው፤ የትናንትናዋ ኢትዮጵያ እየተቀየረች በመሆኑ ሳይረፍድባቸው ከአሁኗ ኢትዮጵያ ጋር መጓዝ ይኖርባቸዋል ሲሉ አመላክተዋል።
በሀብተሚካኤል ክፍሉ
#EBC #EBCdotstream #PMOEthiopia #projects #koysha