Search

ሰዎች በፈተና እና ምክንያት ታስረው የሚቆሙ ከሆነ፣ ሀገርን መሥራት ቀርቶ ቤተሰብን መምራት ይቸገራሉ - ጠቅላይ ሚኒስር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ዓርብ ጥቅምት 14, 2018 32

በርካታ ሰዎች በፈተና መካከል እንዴት ታላላቅ ፕሮጀክቶችን መፈጸም እንደሚቻል እንደሚጠይቋቸው የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ይህን በምሳሌ ሲያብራሩ ምላጭ ፀጉር እና ጥፍርን በየጊዜው ቢቆርጣቸውም ዕድገታቸውን እንደማያስቀር ተናግረዋል።
ሰዎች ከፈተና ውስጥ ዕድል እየፈለቀቁ መሄድን ካላወቁበት፣ በፈተና እና ምክንያት ታስረው የሚቆሙ ከሆነ፣ ሀገርን መሥራት ቀርቶ ቤተሰብን መምራት ይቸገራሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ የኢትዮጵያ ፈተና እየጨመረ እንደሚሄድ ሁሉም መገንዘብ እንዳለበት መልዕክት አስተላልፈዋል።
እስከ አሁን የተሠሩ ታላላቅ ፕሮጀክቶች ስኬታማ የሆኑት ፈተና ሳይገጥማቸው ቀርቶ ሳይሆን ከፈተና ውስጥ ዕድል ማውጣት ስለተቻለ እንደሆነ ጠቅሰዋል።
 
ትላልቅ ሀገራት ጭምር ከኢትዮጵያ የባሰ ፈተና እንዳለባቸው አንስተው፣ እነሱ ግን ፈተናዎቹን ወደ ዕድል በመቀየር የማለፍ የዳበረ ልምድ ስላዳበሩ ወደኋላ እንደማይመለሱ ገልጸዋል።
ፈተናን ወደ ዕድል ለመቀየር በዕይታ ለውጥ ሥራዎችን መሥራት እንደሚገባ፣ ነገር ግን ሁሉም ሰው ከውስጥ ማየት ካልቻለ ዓይን ስላለው ብቻ ዕይታው ይለወጣል ማለት እንደማይቻል ተናግረዋል።
በለሚ ታደሰ