Search

ከኢትዮጵያ አልፈው አፍሪካን ቀና የሚያደርጉ ሜጋ ፕሮጀክቶች

ቅዳሜ ጥቅምት 15, 2018 34

ኢትዮጵያ ከሕዳሴ ግድብ መመረቅ በኋላ ይፋ ያደረገቻቸው እና በቅርቡ ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች የሕዝቡን የልማት ጥያቄ ከመመለስ ባሻገር ባህልን እየፈጠሩ ነው፡፡

በተለያየ መንገድ ተጀምረው የሚጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ጀምሮ መጨረስ እንደሚቻል ያሳዩና በሀገሪቱ የግዙፍ ፕሮጀክቶች አስተዳደርም አዲስ ባህልን እየፈጠሩ የሚገኙ ናቸው፡፡

ከእነዚህ ሜጋ ፕሮጀክቶች መካከል ኢትዮጵያ ለዘመናት ማሳካት ያልቻለችው የተፈጥሮ ጋዝ ማምረት መጀመሯ፣ አዲስ እሳቤ የሆነው የኒውክሌር ቴክኖሎጂ ውጥን እንዲሁም የአፈር ማደበሪያ ፋብሪካ ፕሮጀክት ለዚህ የሀገሪቱ እንቅሰቃሴ ተጠቃሾች ናቸው፡፡

እነዚህ በዕቅድ ተይዘው ተግባራዊ እየተደረጉ የሚገኙት ሜጋ ፕሮጀክቶች ከሀገር አልፈው አፍሪካን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስለመሆናቸው ብዙኃኑ ይስማሙበታል፡፡

ኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኢንደስትሪ አብዮት ሲጀመር ዘመናዊነትን መቀላቀል የቻለች ሀገር ብትሆንም፤ በዘመኑ የነበረውን ለውጥ በቅጡ መረዳት ባለመቻሏ ዓለም ወደ ፊት ሲገሰግስ ወደ ኋላ ቀርታለች፡፡

አንዱና ትልቁ ስብራት የሆነው በነበሩ የመንግስታት ለውጦች ውስጥ የሀገር ሐብቶችን አውጥቶ መጠቀም ባለመቻሉ ኢትዮጵያ ከድህነት መላቀቅ ሳትችል ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡

አሁን ኢትዮጵያን ከኢትዮጵያውያን ውጪ የሚታደጋት አለመኖሩን በመረዳት ይህ ትውልድ ድህነትን በመጠየፍ ከጉስቁልና ልምምድ የሚሻገር መንገድን ጀምሯል፡፡

የበለፀገ ሀገር እና ህዝብን ለመፍጠር እንዲሁም እያንዳንዱን ዜጋ ካለበት የድህነት አረንቋ ለማላቀቅ እንቅልፍ አልባ ጉዞ ተጀምሯል፡፡

በትጋት እና በስራ ብቻ የምትበለፅግ ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ኢትዮጵያውያን ያለፈው ስኬት ሳያዘናጋቸው ከሀገር አልፈው ለመላው አፍሪካ የሚጠቅሙ ሜጋ የሆኑ ፕሮጀክቶችን በመንደፍ እና ጀምሮ የመጨረስ ተምሳሌትነታቸውን ለማረጋገጥ ወደፊት በመገስገስ ላይም ይገኛሉ፡፡

በንፍታሌም እንግዳወርቅ  

#ebc #ebcdotstream #Ethiopia #megaprojects