Search

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምላሽ እና ማብራሪያ ይሰጣሉ

ማክሰኞ ጥቅምት 18, 2018 194

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ይሰጣሉ።
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ይካሄዳል።
በመደበኛ ስብሰባው ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ምላሽ እና ማብራሪያ ይሰጣሉ።
ምክር ቤቱም የመንግሥትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽኑን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
በምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች እና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ ተጠሪዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙ ምክር ቤቱ አስታውቋል።
Ethiopian Broadcasting Corporation (ኢቢሲ) የስብሰባውን ሙሉ ሂደት ኢቲቪ ፓርላማ ቻናልን ጨምሮ በሁሉም የብሮድካስት እና የዶትስትሪም ማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ አማራጮች በቀጥታ ስርጭት ለሕዝብ ያስተላልፋል።