Search

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ካቀረቧቸው ጥያቄዎች መካከል፦

ማክሰኞ ጥቅምት 18, 2018 272

👉🏾የሕዝብ እና የመንግሥትን የሰላም ጥሪን ባለመቀበል የሕዝብን ስቃይ እያበዙ ያሉ ኃይሎችን
አደብ ለማስገዛት መንግሥት ምን ለመሥራት አስቧል?
👉🏾ትግራይ ክልል ወደ ሰላም ተመልሶ ልማት ውስጥ እንዲገባ ምን እየተሠራ ነው?
👉🏾የተጀመረው ሀገራዊ ምክክር ውጤታማ እንዲሆን ከማን ምን ይጠበቃል? በዚህ ረገድ
የመንግሥት አቋምስ ምንድን ነው?
👉🏾የተጀመሩ ፕሮጀክቶች ለሀገር ያላቸው አጠቃላይ ጠቀሜታ እና የመኖሪያ ቤት ግንባታን
አስመልክቶ መንግሥት የያዘው ዕቅድ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ቢሰጥ፣
👉🏾የአገልግሎት አሰጣጥን ለማፋጠን እና የፍትህ ሥርዓቱን ቀልጣፋ በማድረግ ረገድ ምን
እየተሠራ ነው?
👉🏾 መንግሥት 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለመገንባት ዕቅድ መያዙን ይፋ አድርጓል። ይህን እቅድ
ለማሳካት በመኖሪያ ቤት ግንባታ ላይ ምን እየተሰራ ይገኛል?
👉🏾የኑሮ ውድነቱትን አሁን ካለበት ለማሻሻል እና ሕገ-ወጦችን በዘላቂነት ለመቆጣጠር ምን
እየተሰራ ነው?
👉🏾የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ውጤታማነት እና የመጪው ጊዜ ተስፋ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ
ቢሰጥ?
👉🏾በባሌ ዞን የተሰራው ድንቅ ሥራ የሚያስመሰግን ነው፤ ይህንን አጠናክሮ ለመቀጠል ምን
እየተሰራ ነው?